• News

 • “ከመንግስት የሚጠበቀው አዝኛለሁ ብቻ አይደለም” 28 December 2017 | View comments

 •   “ከመንግስት የሚጠበቀው አዝኛለሁ ብቻ አይደለም”
                 አቡነ ቀውስጦስ

     የሠላም ባለቤት እግዚአብሔር ነው፡፡ ለዚህም በሃገራችን ሠላም እንዲሠፍን ፈጣሪን በምህላ ፀሎት እየለመንን ነው፡፡ የኛ ትልቁ መሣሪያችን ይሄ ነው፡፡ አደራ ተሠጥቶታል የተባለው መንግስት ደግሞ ሃገሪቱን በእኩልነት መምራትና ማስተዳደር አለበት፡፡ አጥፊዎችን ለህግ እያቀረበ ስርአት ማስያዝ አለበት፡፡ ተጎጂዎቹን ደግሞ ቦታ ቦታ ማስያዝ ይገባዋል፡፡ ዝም ብሎ ከዳር ሆኖ እንደ ማንኛውም ሰው አዝኛለሁ ቢል አይሆንም፡፡ ሃላፊነትና ግዴታ አለበት፡፡ እንደ ሌላ ሃገር መንግስታት፣ እሱም አብሮ የሃዘን መግለጫ ማስተላለፍ አይጠበቅበትም። ሃዘኑ እንዳይደርስ የመከላከል ስራ መስራት ግዴታው ነው፡፡ አንድነትን ማፅናት ስራው ነው፡፡ ድሮም የተፈራው ይህ አይነቱ ግጭት እንዳይመጣ ነበር፡፡ በጎጥ መለያየት ጥሩ አይደለም፤ጥንቃቄ ይደረግበት ስንል ጮኸናል፡፡ የፈራነው ነው እየደረሰ ያለው። አሁንም ሳይስፋፋ መከላከል ያስፈልጋል፡፡ የዚህ ሃላፊነት ያለበት ደግሞ መንግስት ነው፡፡
   አዝማሚያው ከተስፋፋ ኢትዮጵያ የለችም ማለት ነው፡፡ እኔ በ1999 ስለዚህ ጉዳይ የፃፍኩት መፅሐፍ አለ፡፡ በወቅቱ አስጊ መሆኑን ተናግረናል፡፡ መንግስት ብሄርን ከብሄር የሚያጋጭ ሥራ መስራት የለበትም፡፡  አንዳንዶቹ ቤተክርስቲያናችንን እያፈረሱ ነው፡፡ ይሄ  ከፈጣሪ ጋር ያጣላናል፡፡ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው እየሆነ ያለው፤ እያለቀስን ነው። መንግስት ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል፡፡
  ይሄን ስንል የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ናቸው እንባላለን፡፡ ይሄ ደግሞ አያዋጣም፡፡ ሃገሪቱ አንድነቷ ፀንቶ፣ ልማት ሰፍኖ፣ ስደተኞች ወደ ሃገራቸው ተመልሰው ማየት ነው ምኞታችን፡፡ ስልጣን የያዘ አካል ደግሞ በሥነ ስርአት መምራት አለበት፡፡
  አጥፊዎችን ችላ እያለ፣ ህዝብን እርስ በእርስ ማፋጀት የለበትም፡

  « Back to archive
 • Leave your comment

 • Name:
   
  Email:
  Comment   
  captcha
  Enter the code shown above: