• News

 • ይድረስ ለሙዚቀኛ ፋሲል ደሞዝ 26 January 2018 | View comments

 • ይድረስ ለሙዚቀኛ ፋሲል ደሞዝ

  ከጌታቸው ረዳ ኢትዮ - ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ

  ማንነቴ የተባለው አዲሱ ሙዚቃህ በስእለ ድምጽ ስመለከት ለሕዝብ ማስተላለፍ ከፈለግከው በዚሁ ሙዚቃህ መልእክት ውስጥ ጋር መካተት የሌለበት አስቀያሚ ስራ ተካትቶአል። መቸም ሆን ብለህ ይህ አስቀያሚ ስራ እንዲካተት አንተ ያደረግከው አይመስለኝም። አዎ እኔ ነኝ የምትል ከሆነ ሙዚቃህ ከታሪክ ጋር የሚጋጭ ነው። ሆኖም አቀነባባሪዎቹ የግንቦት 7 ሻዕቢያ አወዳሽ ሆኖ እንዲቀር ያደረጉትን የሻምበል በላይነህ (የዛሬ አያደርገው አገራዊ ተብሎ በሁላችን ሲወደስ ሲወደድ የነበረው ሙዚቀኛ) የሰለቡትን የሙዚቃ አቀነባባሪዎች አንተንም በተመሳሳይ ሰልበውህ ከሆኑ ከነሱ የሚጠበቅ አንዴ የገቡበት አስቀየጣሚ ስራ ስለሆነ ታሪክ ይፋረዳቸዋል።

  የስእሎቹ ቅንብር ያንተ ቅንብር ከሆነ ግን ምንም እንኳ በሌሎች ስራዎችህ የማደንቅህ ብሆንም በዚህ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳለን እኔ እና ጥቂት ወዳጆቼ በስልክ ተነጋግረን ስሕተትህ እንድታርም ካልሆነ ስሕተት መስራትህን እንዲረዳህ አንድ መልእክት እንድናስተላልፍልህ ስለወሰንን ይህ ትችት እንድታነብ በወዳጀቼ እና በኔ ስም ይኼው።

  ፖለቲከኞች መልእክት ለማስተላላፍ የቀለለ መንግድ ሙዚቃ መሆኑን ያውቃሉ። ስለሆነም በፖለቲካ ያልበሰሉትን ሙዚቀኞችን የመስለብ ስራ በማከናወን በሙዚቀኞቹ በኩል መልእክታቸው በቀላሉ እንዲተላለፍ ያደርጋሉ። ሙዚቀኞቻችን ባብዛኛዎቹ (ከጥቂት በስተቀር) የጮሌ ፖለቲከኞች ሰለባ እየሆኑ በብዛት የታየበት ዘመን ወያኔ ወደ ሥልጣን ከመጣበት ወቀት ጀምሮ ካሁን በፊት ባልታየ መልኩ በርካታ ሙዚቀኞችና የሃይማኖት ዘማርያን እንዲሁም ሰባኪያን ሰለባዎች ሆነዋል። አንተ ከዚህ “ከብረዛው” ሁሉ በጣም የራቅክ ብቻ ሳይሆን በህይወትህ ጭምር የከፈልክ ጀግና የኪነት ሰው እንደነበርክ እመሰክራለሁ። በቅርቡ ግን ሻምበል በላይነህን የተጠናወተው የፖለቲካ በሽታ በዓይነቱ ካንተው ትንሽ ለየት ቢልም በሌላ መልኩ አንተም የጮሌ ፖለቲካ አቀነባባሪዎች (ምናልባት) በኩል ሊያጠቃህ የመጣ የፖለቲካ ሰለባ የሆንክ ይመስላል።

   

  በዚሁ ‘ማንነቴ’ የሚለው አዲሱ ሙዘቃህ ውስጥ ያለኝን ቅሬታ ምንድ ነው?

  ሲጀምር የሙ ዚቃህ ርዕስና መልእክት “ማንነቴ” ይላል። ማንነትህ ደግሞ በአርንጓዴ፤ ቢጫ እና ቀይ ሕብር ያለውን ባለ ሦስት ሕብሩ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ የሆነውን መገለጫህ መሆኑን መልእክት ስታስተላልፍ። አበሮ ከመልእክትህ የተቀላቀለው አስገራሚው መልእክት ደግሞ ይህንን ማንነትህን የተጠየፈው የነገድ ፖቲካ አቀንቃኙ ዛሬ እስር ቤት ውስጥ ያለው <ጸረ አማራው> “ በቀለ ገርባ” ን በዚሕ ስእለ ድምጽ ሙዚቃ ቅንብርህ ውስጥ በማካተት ህ እኔን እና መሰል ጓዶቼን እንድንገረም አድርገሃል። ምናልባትም የበቀለ ገርባን ፎቶ በሙዚቃህ ውስጥ እንዲጨመር ባንተ አሳሳቢነት እንዲካተት እንዳልተደረገ አምናለሁ (ተስፋ አደርጋለሁ)። ስለሆነም በዚህ ግሩም የሙዚቃ እና የማንነት ቅንብር ላይ አማራን እና ሰንደቃላማውን የሚጸየፍ በቀለ ገርባን ማካተትህ ከፍተኛ ስሕተት ፈጽመሃል።ይቅር የማይባል ስሕተት (ምናልባትም የታሪክ ወንጀል) ፈጽማሃል።

  በ ቀለ ገርባ ከወያኔ እስርቤት ከተፈታ በ ኋ ላ አስቃባጮቹን ለማነጋጋር ከ2 አመት ተኩል (2015 በፈረንጆች ዘመን አቆጣጠር) በፊት እዚህ አሜሪካ አገር መጥቶ በነበረበት ጊዜ ፎቶ ሊያነሱት ሲሉ ፣ ከጀርባም የኢትዮጵያ ባንዲራ ስለነበር ( ባክ - ግራውንድ ) ሊገባ መሆኑን የተረደው በቀለ ገርባ ፎቶ አንሺዎቹን “ አይ እኔ ከዚህ ባንዲራ አጠገብ ፎቶ አልነሳም ” ሲል እምቢታውን እንደገለጸ በወቅቱ መነጋጋሪያ ሆኖ መሰንበቱን ይታወሳል። በዚህ ላይ ጥቂት አገር ወዳድ ሃያሲያን የተቸንበት መነጋገሪያ ነበር። አንተ “የማንነቴ” መገለጫ ብለህ በኩራት ያሸበረቅክባትን ሰንደቃላማችንን ነው በቀለ ገርባ የተጠየፋት። ለይግረም ዛሬ ከተጠየፋት ሰንደቃላማ ጋር አያይዘህ ስለዚህ ጸረ አማራ ምሁር፤ ባልዋለበት ‘አገር ወዳድነትና ሰንደቃላማ አክባሪነት” ተቆነጃጅቶ በስእለ - ድምጽ ሙዚቃዊ ስራህ መያያዙ እጅግ አስቀያሚ ስራ መሆኑን እንድታውቀው።

  በቀለ ገርባ ጸረ አማራ ነው።

  ሻምበል በላይንህን በመናኛ እና አሳፋሪ ፖለቲካቸው ሰልበው በሙዚቃ ስራው ላይ (ወዳጃቸው ሌንጮ ለታንና የሌንጮ ባንዴራ ለምን እንደረሱት ባይገባንም) የሌንጮ ለታ ጥብቅ ወዳጆች፤ እና “ዘመነ ካሴ”ን የከዱ የገዛ ታጋያቸው ሕይወት ያበላሹ/ አሰቃይዎቹ/ እነ ብርሃኑ ነጋ፤አንዳርጋቸው ጽጌ እና ጸረ አማራው በቀለ ገርባ፤ ሙዚቃው ቅንብር ውስጥ ተካትተው ሕዝብ እንዲያመልካቸው ሻምበል በላይነህ ሙዚቃ እንዲካተቱ የሰለቡት ዲሲ ውስጥ ያሉት ታዋቂዎቹ የብርሃኑ ነጋ ወዳጆች “የግም - ኪነ” ሙዚቃ አቀነባባሪዎች አንትንም ሰልበውሃል የሚል ጥርጣሬ አለን።ወድ ሙዚቀኛ ፋሲል ደሞዝ ‘አማራነት’ ስለ ‘ኢትዮጵያዊነት’ መስበክ ማለት በቀለ ገርባን ማቆነጃጀት አይደለም።

  ገጣሚው ወጣቱ ሔኖክ የሺ ጥላ ስለ አማራነትና ኢትዮጵያነት እንዲህ ይገልጸዋል።

  " ስለ ኢትዮጵያዊነቴ ዛሬም ነገም ፣ እሰብካለሁ ። የማምንበትም ምንነቴ ነው፣ ማንነቴ ነው ፣ የማልፍቀው ፣ በክልል ባንዲራ የማልቀይረው ። ሳልፈልግ ተገድጄም ቢሆን ማነስ አልችልም ፣ አንደኛ ኢትዮጵያዊ ነኝ ፣ በዛ ላይ ደሞ አማራ ነኝ ( ይሰማል ወይ ?)" ይላሃል ወታዩ ሔኖክ የሺጥላ።

  ሔኖክ < ሳልፍልግ ተገድጄም ብሆን ማነስ አልችልም። ማንነቴን በክልል ባንዴራ የማልቀይረው። ” ሲል በቀላል እና ግልጽ አማርኛ ነግሮናል። አንተ ወንድሜ ፋሲል ደሞዝ ግን ተገድደህም ይሁን ምክንያቱን ባልገባን ሁኔታ ኢትዮጵያዊነትን በክልል ባንዴራ የቀየረው በቀለ ገርባን በማቆነጃጀትህ “ አንሰህ ” አይተንሃል።የፈለገው ሊያቆነጃጅህ ሊቃወመን ይችላል። በእኔ እና በጓዶቼ ዓይን ግን በዚህ በዛሬው አዲሱ ሙዚቃህ አንሰህ አይተነሃል። ስለ በቀለ ገርባ ምን ብሎ ስለ አማራ እንደተናገረ ካሁን በፊት በተቸሁት ጽሑፍ በሰፊው ተገልጿል። አሁን ግን ሔኖክን አስደግፌ ስለ በቀለ ገርባ ያለውን ልጥቀስ፡

  << እንደውም አንድ ጨዋታ ላጫውታችሁ ። ኦቦ በቀለ ገርባ ሰሞኑን አማሪካን ሀገር መጥተው ፎቶ ሊነሱ ሲሉ ፣ ከጀርባም የኢትዮጵያ ባንዲራ ( እንደ የጀርባ መሰረት ) ( ባክ - ግራውንድ ) ሊገባ መሆኑን የተረዱት ኦቦ በቀለ ገርባ ፣ << አይ እኔ ከዚህ ባንዲራ አጠገብ ፎቶ አልነሳም !>> አሉ አሉ ። እንግዲህ ፣ ሰው ተምሮ ፣ ተምሮ ፣ ተምሮ ፣ ተምሮ ( እደግመዋለሁ ፣ ተምሮ ተምሮ ) ፣ እንደዚህ እንደሚያስብስ አስባችሁ ታውቁ ይሆን ? በጣም የገረመኝ ደሞ ፣ እኝህ “ ትልቅ ሰው ” ( በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ነው ) ሲታሰሩ፣ እኔን ጨምሮ ፣ ለሳቸው ያልጻፈ ፣ ያልተናገረ ፣ ይኖራል ? ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረ ማሪያም ፣ እስከ ታማኝ በየነ እና ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ መስፍን ወልደ ማርያም እና ወዘተ ።>> ይላል ሔኖክ የሺጥላ። ይህ የተማረ፤ትልቅ ሰው << አይ እኔ ከዚህ ባንዲራ አጠገብ ፎቶ አልነሳም !>> አሉ አሉ።አንዲህ ያለ የተማረ ሰው እንዴት ወደ እዚህ ዓይነቱ ድንቁርና ሊገባ ቻለ? ሲል ነው በአግራሞት የተገረመው።

  ሔኖክም እኛም እንደ መገረማችን እና ለበቀለ ገርባ ድንቁርና መልስ ፍለጋ ጠይቀናል። ታዲያ የኛ ሙዚቀኞች የጮሌ ፖለቲከኞች ሰለባ እየሆኑ ከግሩም የሙዚቃ ስራቸው ውስጥ ከሙዚቃ ቅንብር መልእክቱ ጋር የማይሄድ “ የእርጎ - ዝምብ” ያህል ስራ በመስራት በሙዚቃ ስራዎቻቸው ውስጥ ጣልቃ እያስገቡ በታሪክ ላይ ወለምታ እያደረሱ ነው።

  ወንድሜ ደምጸ መረዋው ፋሲል ደሞዝ ሆይ!

  በቀለ ገርባ በሰንደቃላማችን ብቻ ሳይሆን፤ ያንተን ማንነት የሰጡህን ወላጆችህ አማራዎች ሳይቀር “ኦሮሞዎችን “ይቅርታ እንዲጠይቁ” የጠየቀ ጉደኛ ጸረ አማራ ሰው ነው። በሳብቨርሲቭ (በብከላ) ፖለቲካ የተጨማለቀው እዚህም ውስጥም ያለው ተቃዋሚ ተብየው ማሕበረሰብ በቀለ ገርባን በፈለጉት ዓይነት “ሮማንትሳይዝ/ እያደረጉ እያቆነጃጁ ለማቅርብ ቢጥሩም የበቀለ ገርባ ማንነት በግድ ‘የአማራ ወዳጅ” ሊያደርጉት አይቻላቸው ም። ከሚከተለው የፖለቲካ ባሕሪ አንጻር ባሕሪው አይፈቅድለትም። በጥላቻ የተበላሸ የኦሮሞው ምሁር በቀለ ገርባ ባንተ ሙዚቃም ሆነ በሻምበል በላይነህም ይሁን በጎንደር ከተማ የታየው ‘በተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፈኛ’ ትዕይንት ባስሰሙት መፈክርም ሆነ ይዘውት በነበሩዋቸው ፎቶግራፎች ውስጥ “ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን” ትተው የበቀለ ገርባ ፎቶ ቢያውለበልቡም፤ የበቀለ ገርባ “ጸረ አማራነቱን” ማሕደር ሊፍቁለት አይ ቻላቸውም፤አይቻላችሁም!በቃ!

  አንባቢዎቼ ሆይ! ሙዚቀኞች እና ሕዝብ እራሱ ጭምር ‘የጮሌ ፖለቲኸኞች እና የሚዲያ ሰለባዎች’ እየሆኑ ችግር ውስጥ ገብተናል። ይህ ጉዳይ አትኩሮት እንዲደረግበት ደጋግሜ ብናገረውም ሰሚ የለም። ለምሳሌ በቀለ ገርባንም ሆነ እነ ሌንጮ እና የመሳሰሉ የነገድ አቀንቃኝ የፖለቲካ በሽተኞች ኢሳት በሚበላው የኢሳያስ አፈወርቅ እና የብርሃኑ ነጋ “የጀርባ መታሺያ ክፍል” (ፊዚካል ቴራፒ ) የሆነው ራዲዮና ቴ/ቪዥን ጣቢያ በተደጋጋሚ ሲያስተናግድ የታዘበው ሰዓሊ አምሳሉ ገ / ኪዳን አርጋው ምሬቱን በ እንዲህ ይገልጸዋል፤ -

  << ኢሳት በተደጋጋሚ ለእነዚህ ወገኖች ዕድል እየሰጠ ይሄንን የተናቀ የተጠላና ውዳቂ የሀገርናንና የሕዝቧን ደኅንነት ህልውና ሉዓላዊነት ጥቅምና ክብር ለአደጋ የሚዳርገውን የፖለቲካ ( የእምነተ አሥተዳደር ) አስተሳሰባቸውን እንዲያስተዋውቁ ሕዝብን አሳስተውና አሰናክለውም ከጎናቸው እንዲያሰልፉ ከዚህም አልፈው የጥፋት ዓላማቸውን ለማሳካት ፈጠራ የተሞላበትንና መረጃ የሌላቸውን እርስ በእርስ የሚያፋጁ ወሬዎችን ወከልነው የሚሉት ብሔረሰብ ሐሳብ እንደሆነ አስመስለው እንዲያወሩና ይሄንን ዕኩይ አስተሳሰባቸውን የማይጋራው አብዛኛው የብሔረሰቡን ክፍል ዕኩይ አስተሳሰባቸውን እንዲጭኑበት ማሳሳት እንዲችሉ እንዲያሰናክሉ ዕድል ሰጥቷል፡፡>>

  የኢሳት ስሕተትና የተጋፈጠው አደጋ – ሠዓሊ አምሳሉ ገ / ኪዳን አርጋው August 28, 2015 ኢሳት በዛው አልተወሰነም። በቀለ ገርባ ኢሳት ላይ ቀርቦ ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት ስለ አማራ የተናገረውን ልጥቀስ፤ እኔ ስለ በቀለ ገርባ ጸረ አማራነትና ጸረ ሰንደቃላማ እና ጠባብ ኦሮሞ አቀንቃኝንት የጻፍኩት ማስረጃዎች የኔ ስለሆኑ የኔውን ለሌላ ጊዜ አስቀምጬ እንደ እኔው የተቆጩ ሌሎች ዜጎች ስለ በቀለ ገርባ የጻፉትን ሙዚቀኛ ፋሲል ደሞዝ እና መሰል ሙዚቀኞች እንዲሁም የበቀለ ገርባ አቀንቃኝ የአንደነት ሃይሎች ነን የምትሉ ሁሉ ይህንን ማስረጃ ተመለክታችሁ በበቀለ ገርባ ያላችሁን የተሳሳተ አምልኮት ብያስጥላችሁ ይረዳ ዘንድ ይህንን ማስረጃ ላቅርብ።

  አቶ በቀለ ገርባ አሁን አሳት ጭረዋል ! ( ሔዋን ማንደፍሮ August 5, 2015)

  << ከኢሳት ጋር የሰጡትን ቃለ መጠይቅ አዳመጥኩ። ከዚህ ሁሉ ዓመት አስራት በኋላ አንዲህ አይነት ብሄርተኝነት የተሞላበት አቋም ይዘው ብቅ አንደማይሉ ትንሽም ብትሆን ተስፋ ነበርረኝ። አስር ቤት ሆነው አብረዋቸው የነበሩት ከተለያዩ ብሄር የተውጣጡ አስረኞች ጋር ከርመው አንዴት ሰው ይህን ያክል ግፍ ቀምሶ ሲወጣ ከዘር ባልወረደ ሃሳብ ተመልሶ ብቅ ይላል ??? አስር ቤት አንደ ሰው አንዲያስቡ የሚያረግ ተስፈ ነበረኝ። ይች ሃገር የማናት በለው ራሳቸውን ጠይቀው ለየት ያለ መልስና አቋም ይዘው ቢወጡ ምን በኮራንባቸው ነበር። መልሰው አዛው ነክረውናል። አማራውን ሕዝብ ሳይሆን የምንወነጅለውን ከዛ ክፍለ ብሄር ወተው በኦሮሞ ህዝብ ላይ ግፍ ያወረዱበት ብለው አስምረውበታል። በተጨማሪም የኦሮሞ ህዝብ በአንድብሄር ስር ተጽኖ ተደርጎብን፤ ተገደን ነበር አማራው ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል አሉ። በሌላው በኩል ውበታችን ልዩነታችን ስለሆነ ግን አንድነት አየተባለ አንድ ቋንቁ ብቻ አናውራ የሚለው አንደማይመቻቸው አስረድተዋል። አኝህ ሰው ለፖለቲካ ፍጆት ካልሆነ አንዲህ ዓይነት ውንጅልና በጣም ደካማነታቸውንና ከማሳየቱም በላይ የፖለቲካል ፍጆታውን ለመቀጠል ቆርጠው የተነሱ የመስላል ። ለምን ?? አንድ ሃገር ከነታሪኩ ከነጉድፉ ይዘን መኖር ካልቻልን አንዴት ልንኖር ነው ?? አማራውን ወክሎ የሚቀርበው ማነው ? ማነው ይቅርታስ የሚጠይቀው ?? ሰጪውስ ማን ነው ?? አማራ ማለት አራሱ ውስጡ ህብረ ብሄር ነው በሃይማኖትም የተለያዩ አምነቶች አሉት። አንዴት ሆኖ ነው አንድ የአማራ መሪ መቶ [ ማንን ወክሎ ?? ይህንን አንኳን አንዴት አቶ በቀለ መረዳት አልቻሉትምን ወይስ አንደው ድብቅብቆሽ ፓለቲካ ? ] አማራ ለማንስ ነው ይቅርታ ሚለው አንደው ጥፈት ተሰራ ተብሎ አንኳን ቢታመንበት ?? ሌላው ደግሞ አማራውስ ተሰራብኝ ያለውን ወንጀል ለኦሮሞ የተባለው ክፍለ ብሄር መቅረብስ የለበትም ? ያ በማስረጃ ከመጣ ኦሮሞን አንወክላለን የምትሉት ለአማራው ሕዝብስ ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ናችሁ ወይ ??>> አቶ በቀለ ገርባ አሁን አሳት ጭረዋል ! ( ሔዋን ማንደፍሮ August 5, 2015 )

  ወንድማችን ሙዚቀኛ ፋሲል ደሞዝ ስለ በቀለ ገርባ ምንነት በጥቂቱ እንግዲገባህ ከላይ የተዘገበው ትችት እንድትገነዘብ አቅርቤአለሁ። እንደምትረዳውም ተስፋ አለኝ።

  በመጨረሻ ላንተም ሆነ አጋሮችህ የኪነት ሰዎች እና የአማራ ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጆች በያላችሁበት አገርም ሆነ ከተማ የምጠይቀው አንድ ነገር አለ። በቀለ ገርባን ብርሃኑ ነጋን፤ አንዳርጋቸው ጽጌን ከአማራ ማንነት፤ ከአማራ ሰልፍ ትዕይንት እና የሙዚቃ ስራዎቻችሁ ጋር እያገናኛችሁ ስታወድሱ በብዙ ንግግሮች፤ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች እና ጽሁፎችን አይተናል፤አንብበናል አድምጠናል። ስለ ኢትዮጵያ አንደነትን ስለ አማራ ማንነት ህይወታቸውን የሰጡትን ክቡር ሐኪም አስራት ወልደየስን እና ሌ ሎ ች አገር ወዳድ አርበኞችን ስታካትቱ አላየንም። እነኚህ ሰማእት በሙዚቃዎቻችሁ ላይ እንዳይታወሱ ስለምን ሆነ? ለምንስ ፎቶግራፋቸው ሳይታይ የነዚህ ጸረ አማራ ግለሰቦች ስታቆነጃጁ መከራችሁን አያችሁ? ይህ ጥያቄ ለጎንደር (ከተማ) ፤ለባሕርዳር፤...ተሰላፊዎች እና እዚህ እውጭ አገር ላሉት ተቃዋሚዎች እና የኪነ ት ሰዎችን ይመለከታል (በጣት የሚቆጠሩትን አይጨምርም)። ለመሆኑ ይህ ስሕተት/ግድፈት (ክሕደት) ስትፈጽሙ የፖለቲካ ጮሌዎች ሰለባ መሆናችሁ ይታወቃች ኋ ል? ወይስ ዛሬም ለወደፊቱም በዛው ልትቀጥሉ ነው? የኚህ ሰማእት አጽም ይወጋናል ብላችሁ ሰግታችሁ ታውቃላችሁ? እነ በቀለ ገርባ፤ የእነ አንዳርጋቸው፤ የእነ ብርሃኑ ነጋ ፎቶ ይዛችሁ ስተቆሙ ስለ አገሪቷ አንደንነት እና ስለ አማራ ሕልውና ህይወቱን ለመስዋእት የሰጠ ሰማእት አስራት ወልደየስና ኢንጂኔር ሃይሉን እንዴት እና በምን ሂሳብ ልታስታውሱዋቸው አልተቻላችሁም?

  ስለ አማራው እሮሮ፤ መብት ፤ ስለ ሰንደቅ፤ ስለ ኢትዮጵያ ክብር መስዋእት የከፈሉትን ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ወይስ በቀለ ገርባ? የሓኪም አስራት ወልደየስም ሆነ የኢንጂኔር ሃይሉ ሻውል ፎቶግራፍ አጣችሁ? ወይስ ሰለባዎች ሁናችሁ ነው? ጎንደሬዎች፤ጎጃሞች የአስራትንና የሃይሉን አስተዋጽኦ አታውቁት ም? ወይስ የሞተ ሞተ ነውና አይነሳም?!!!!! ትግሬዎች መቀሌ ውስጥ የባንዳው መሪያቸው የመለስ ዜናዊ ፎቶግራፍ በየግሮሰሪው፤ በየሱቅ ቤቱ ደጃፍ ከክርስቶስ፤ከተዋናዮች፤ከሞዴሎች መሃል ተደርድሮ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እና እንደ ቁርዓን፤እንደ ዑንቅ፤ በውድ ዋጋ ሲሸጥ እና ሲገዛ ስለ እናንተው እና ስለ እኛ ብለው ለተሰው በርካታ ብጹአን እነ አስራት እነ ሃይሉ......እንዴት ልትረሱዋቸው ቻላችሁ?!! በምትካቸው በቀ ለ ገርባን? በምን ሒሳብ?! ለሟቾቹ አጽም ባትፈሩ ኢትዮጵያን እና ታሪክዋን አትፈሩም! አጼ ቴዎድሮስ ስታመሰግኑ የዘመናችን ቴዎድሮሶችንስ ፈልጋችሁ አጣችሁ? በቀለ ገርባን ነው የዘመናችሁ ቴዎድሮስ? ከቴዎድሮስ ጋር አዋህዳችሁ የዘፈናችሁለት እኮ በቀለ ገርባን ነው? ፋሲል ይህንን ጉድ እስቲ ቁጭ ብለህ አስብበት! ምንምስ ቢሆን ውለታውን ብትዘነጉትና ብትረሱት ምናለበት ለናንተ እና ለአገሩ ሲል ኤርትራና ሶማ ሌ ሄዶ ከጠላት ጋር ተዋድቆ መስዋእት የሆነው በሺ የሚቆጠር ሰራዊት የውግያ ማሕደርና ፎቶግራፎችን ሙዚቃዎቻችሁ ውስጥ የሚካተት አጣችሁ? ጠላት ኮረብታ ላይ ቆሞ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ተክሎ ሲያውለበልብ የሚያሳይ ሃቀኛ የሠራዊታችን ነባር ፎቶግራፎች መኖራቸውን እንዴት አታውቁም? እነዚህ ናቸው ወይስ በቀለ ገርባ የቴዎድሮስን ጽዋ የተቀበሉ? ዋ ምፅዋ! የሚለው መጽሐፍ ላይ የተጠቀሱት ጀግኖች የቴዎድሮስን አርአያ ተከትለው በገዛ ሽጉጣቸው እየጠጡ ለዘላለሙ የተሰናቡ የእምየ ኢትዮጵያ ልጆች እንዴት በበቀለ ገርባ ሊተኩ ቻሉ? ወንድሜ ፋሲል! ስሕተትህ ይገባሃል? የኔ ወንድም! እስኪ በሕሊናሕ አስብ የምጽዋ ተጋድሎ፤ ‘ያስለቅሳል! ያስለቅሳል ብቻ? እምባ እምባ ያሰኛል! ይተናነቃል፤አቅል ያሳጣል፤ የቊጭቱ ንዳድ አንጀት ያቃጥላል!

  ውድ ወንድሜ ሙዚቀኛ ፋሲል ደሞዝ

  ላለፈው ብልሸት ምን ይደረግ፤ የፈሰሰ ውሃ አ ይታፈስ፡ ለወደፊቱ ግን የፖለቲካ ሰለባ ላለመሆን ጥንቃቄ አድርግ። እንደ ሻምበል በላይነህ የሙዚቃ “ድግስ” ላይ ማዕቀብ እንዲደረግበት እንደጠሩበት ወገኖች ባንተ ላይም በቀለ ገርባን በመጨመርህ ማዕቀብ እንዳይደረግብህ (ሳታወቅ ከሆነ) ስህትትህን ይቅርታ ጠይቀህበት ለወደፊቱ ሙዚቃዎችህን በጥንቃቄ እንደምትሰራቸው ተስፋ አደርጋለሁ። የፋሲል ማንነቴ የሙዚቃ ስራ ለማየት ይህንን ይመልከቱ።

  Fasil Demoz - Manenete | ማንነቴ - New Ethiopian Music 2018

  https://youtu.be/Riox5xJ9wc4

  አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ እና “የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው” የሚለው አዲስ መጽሐፍ እና ሌሎች የአማርኛ እና ትግርኛ መጽሐፍቶች ደራሲ እኔን ለማግኘት የምትሻ ከሆነም ስለኬ (408) 561 - 4836 ነው መልእክት መተው ትችላለህ።

  « Back to archive
 • Leave your comment

 • Name:
   
  Email:
  Comment   
  captcha
  Enter the code shown above: