• News

 • የአማራው ትግልና ግንቦቴዎቹ 17 August 2018 | View comments

 •  

  የአማራው ትግልና ግንቦቴዎቹ

  (ከጋሻው ቀለሙ)

  የፖለቲካ ሙቀት መለኪያ መሳሪያ ቢኖር አንዱ ሌላዉን የሚበልጥበትን ለማወቅ መለካት ያስችለን ነበር። በ ኢትዮጵያ ያሉት ድርጅቶችና ፖለቲከኞች ግን መመዘኛ ሚዛኑን እንኳን ከጥቅም ዉጭ ያደረጉ ናቸው ቢባል አያስገርምም። አንዳ ንዶቹ እንዲያዉም ተነቃባችሁ ሲባሉ ማፈሩ ቀርቶ የበለጠ ለማታለልና ሁልጊዜ ሕዝብን ለማሞኜት፤ ዘዴያቸዉን እየቀያየሩ ምላሳቸዉን አሹለውና ሆዳቸዉን በእጃቸው ጨብጠው የህዝብን ጥቅም ሳይሆን የእራሳቸዉን ኪስ ለመሙላት የተሰለፉ መሆናቸው ን ከቀን ቀን አያሳዩን ነው። አሁን የኢትዮጵያ ፖለቲካ እየሰከነና የኢትዮጵያ ህዝብም እፎይ ለማለት ሲጀምር ደግሞ እነዚህ የዘመኑ የሆድ ቅጥረኞችና አቀንቃኞች ተመልሰው ብቅ ብለው እንጠቀምባችሁ ማለታቸዉን አላቆሙም። እስኪ ከብዙዎቹ ዉስጥ በግልጽ ቁጭ በሉና ላ ሞኛችሁ የሚሉንን እንመልከት። ዛሬ የማተኩረው ግንቦት 7 በሚል ስም የተሰባሰቡትን በዶክተር ብርሃኑ የሚመራዉን ድርጅት ነ ኝ ባይ በሚሰራው ላይ ይሆናል። የዚህ ቡድን አመራሮች በኢትዮጵያውያን ትግል ላይ ስራየ ብለው ሲሞቅ በረዶ እየጨመሩ የሚያ ካሂዱት ፖለቲካ በእዉነት እነዚህ ሰዎች ጤና አላቸው? ያሰኛል። መዥገር የከብቱ ጭራ ወይም አፉ ከማይደርስበት የሰዉነቱ ክፍል ከተጣበ ቀ የከብቱን ደም እየመጠጠ ይዎፍራል እንጅ መልቀቂያ የለዉም። በእኔ አመለካከት ግንቦት 7 የሚባለዉም እንደዚሁ ሆኖብኛል። የዶ/ር ብርሃኑን ነገር አዉርቸ አልጨርሰዉም፤ በእርሱ የሚመሩትና አብረው አመራር ነን የሚሉት ስራቸዉን ለማያዉቅ ሰው ለተወሰነ ጊ ዜ አታለሉ እንጅ ለእንደኔ አይነቱ የእነርሱን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሮ ለተከታተለ ሁሉ በኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ላይ የሚሰሩትን አሻጥር ለማዎቅ ጊዜ አልፈጀብንም። ሕዝብ እንዳይታለል በተቻለ መጠን ባለፉት መጣጥፎቻችን ብዙ ስንል ቆይተናል። ግንቦት 7 እንዴትስ ተቁ ቋመ? ለምን ተቁቋመ? ለማን ተቁቋመ? የሚሉትን ጥያቄዎች ወደ ኋላ ሂዶ ላጠናቸው ብቻ ነው ይህ ድርጅት ምን እ ንደሆነ የሚገለጽለት።

  በመጀመሪያ ስለ ግንቦቴዎቹ በጥቂቱ፤

  የዶ/ር ብርሃኑ የዉስጥ ለዉስጥ ስራ የጀመረው አሁን በዎያኔ ብቻ ሳይሆን ከዚያም ቀደም ብሎ ነበር። የሰዉየዉ ጸባይ ሲገለጽ ከመጣዉ አላፊ ባቡር ለመሳፈር ጊዜን የማይጠብቅ ሰው እንደሆነ ማንም የሚያዉቀው ጉዳይ ነው። ይህም ጸባዩ ወያኔን ለማጠናከር ሲል ብቻ ከዉጭ ሐገር ተቀጥረው ከገቡት አንዱና የመጀመሪያው አድርጎታል። ዎያኔ እንደገባና ስልጣኑ ን እንደተቆናጠጠ ድሃይቱ ሃገራችን በሌላት ገንዘቧ ከብክባ ያስተማረቻቸዉን እዉቅ ምሁራን ከአዲስ አበባ ዩኒቬርስቲ ስያባርሯቸው ዶ/ ር ብርሃኑ ነበር በሽሚያ ቦታቸዉን የተረከበው። በሌላ በኩልም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌም ከወያኔ ጋር በመሆን የአዲስ አበባ አስተዳ ደር ዉስጥ ተሿሚ ሆኖ ያን የፈረደበትን ኢትዮጵያዊነት ብሎም አማራዉን ከወያኔ ጋር አብሮ እንደወረደ ሲወርፍ የነበር ሰው ነው። “አንድ ሰው ብሄሩን ሲጠየቅ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለምን ይላል፤ ለምን ብሄሩን ከመታዎቂያዉ ላይ አይገልጽም" እያለ በተለይም አማራውን ከወያኔ በበለጠ ሲሰድብ ቆይቷል። ይህን ማዎቅ ለፈለገ “የአማራ ህዝብ ከየት ወደ የት” በሚል ርእስ በዎያኔ ሊወደስ የሞነጫ ጨረዉን ትርክት ፈልጎ ማንበብ ይችላል። ሌላው ቄስ ኤፍሬም ማዴቦ የሚባለው የግንቦት 7 አመራር ደግሞ በየቦታዉ እየሄደ አማራን ሲዘልፍና በስብሰባ ሲሳለቅ የኖረ ነው። ለአማራው የወያኔው ግድያና ዘለፋ አልበቃ ብሎት ይህም ሰዉ አማራዉን እንደ ጠላት “አማራን ልክ አስገብተነዋል ገናም እንዳይነሳ ነው የምናደርገው” ብሎ በየስብሰባው ትንሽ ሳይሰቀጥጠው ሲለፍፍ የኖረ ሰው ነው። ይህን በጥቂቱ ለመግለጽ ሲባል ነው እንጅ ሊሎችም እንደ ንአምን ዘለቀና አበበ ቦጋለ የሚባሉትም አብረው ሲሳደቡና አማራን ሲያንቋሽሹ የነበሩ ናቸው ።

  ኢትዮጵያ የሚል ድርጅትን የማፍረስ አባዜ፡

  የእነ ዶ/ር ብርሃኑ አመጣጥና አወጣጥ ከመጀመሪያዉም ድርጂትን በማፍረስ የተካነ ነው። ነገሩ ጓደኞችህ ን ብትንገረኝ ማንነትክን እነግርሃለሁ እንደተባለዉ አባባል ነው። ዶ/ር ብርሃኑ ከኢሕአፓ ጋር አባል በነበረበት ጊዜ በድርጂቱ ላይ አላስፈላጊ አሻጥር ሲሰራ ቆይቶ በኋላም እሸሻለሁ ሲል ተይዞ በኢሕአፓ እስር ቤት ዉስጥ ብዙ ጊዜ ታስሮ የተባረረ ጓዶቹን የከዳ ከሃዲ ለመሆኑ ብዙዎቹ በጊዜው የነበሩት ስለሚያዉቁት በዚሁ ልለፈው። ቀጥሎ ኢትዮጵያዉያን በነቂስ ወጥተው የመረጡትን ቅንጅት የአማራ ድርጅት ነው ብለው እንዴት እንዳፈረሱት በጥቂቱ ላስረዳ። በኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚታዎቁት ድርጅቶች ዉስጥ ቀንደኛ ኢትዮጵያዊ ድርጅት መኢአድ ለመሆኑ አገር ያወቀው ጉዳይ ነበር። ከምርጫው በፊት ወያኔ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ተልኮ የመጣ በ መሆኑና መኢአድም ኢትዮያዊነቱን አጉልቶ ስላቀነቀነ በወያኔ በኩል መጥፊያው የሚፈለግለት ድርጅት እንደነበር ሕዝቡ የሚያዉቀው ሐቅ ነው። እንኳን ወያኔ ፈረንጆቹም የኃይሉ ሻዎልን መኢአድ ከነመሪዉ ለመደምሰስ ተሰልፈው ነበር ቢባል ስህተት አይደለም። ሁሉም መኢአድ እንዳይቀጥል የፈለጉበት ምክንያት ግልጽ ነበር። ይኸዉም ምንም እንኳን መኢአድ ዉስጥ ያሉት ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተወከሉ ቢሆንም ባል ዋለበት የአማራ ድርጅት ነው ተብሎ ስለተፈረደበት ብቻ ነበር። መኢአድን በዘዴ ለማጥፋት ሲፈለግ አለን ያሉት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና አንዳርጋቸው ጽጌ ከጥቂት ግብረ አበሮቻቸው ጋር ሆነው ነበር። መጀመሪያ ገብተን እናፍርሰው ከ ሚል አስተሳሰብ ተነስተው ከምንም የማይገባ አባል የሌለዉን ድርጅት ቀስተ ዳመና ብለው ፈጠሩ፤ ቀጥለዉም ከመኢአድ ጋር ግንባር ፈ ጠርን ብለው ገቡና ግንባሩም ቅንጀት ተባለ። ትልቁ የመኢአድ ስህተትም ከዚህ ላይ ነበር። ከዚያም ያዉ ሌሊት ሌሊት ከነበረከት ስ ምኦን ጋር እይተሞዳሞዱና ቀን የሚሰራዉን ነገር ሁሉ ለወያኔ እያስረከቡ ቆይተው ቅንጅትን አፈረሱ። እንግዲህ እኔ አንባቢን ላለ ማሰልቸት አለፍ አለፍ አያልኩ እንደምገልጽ ይታይልኝ። በተለይም ቅንጅትን በማፍረስ የተቀናባበረዉን የወያኔና የስርጎ ገቦቹን የነብ ርሃኑ ነጋን ነገር የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ የተመለከተው መሰለኝ። ሆኖም ግን ቅንብሩ እንዴት እንደሆነ እስከ አሁን ድረስ ያልገባቸው የዋህ ኢትዮጵያዉያን እንዳሉ ልብ እላለሁ። ቅንጅትን ያፈረሱት ኢትዮጵያ ዉስጥ ብቻ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው። እኔ ግን እንደተከታተል ኩት ያፈረሱት ብርሃኑ ነጋ፤ መስፍን ወልደማርያምና ልደቱ ከዉስጥ፤ አንዳርጋችው ጽጌና እነ ኤፍሬም ማዴቦ ደግሞ በዉጭ ሃገር ሆነው ነበር። ይህን ሁሉ ደግሞ በገንዘብና በቁሳቁስ እየረዱ እንዲፈጽሙ የሚያደርጓቸው ወያኔና ዉስጥ ለዉስጥ የሚሰሩ የኢትዮጵያን ሰላም የማይፈልጉ የዉጭ መንግስታትም ነበሩ። ይህን ለታሪክ እንተወዉና የዚህ ሁሉ ዒላማ የነበረው ግን ያው የፈረደበት ኢ ትዮጵያን ከደሙ ጋር የቀላቀለው አማራ ብቻ ነበር። ይህንንም በግልጽ ያየንበት ቅንጅትን እንዳፈረሱ የአሜሪካ መንግስት እንኳን ለነብርሃኑ ነ ጋ አዲስ አበባ ባለው የአሜሪካ ኤምባሲ በኩል አሜሪካ እንዲመጡ ቪዛ ሲያድል ኃይሉ ሻዎል እንዳይመጣ ቪዛ ተከልክሎ ነበር። የዚህን የኢትዮጵያን ሕዝብ መከፋፈል ትልቅ ቅንብር ብዙው ኢትዮጵያዊ ዉስጡን መርምሮ አልተመለከተዉም ማለት እችላለሁ። በአጭሩ ለማ ጠቃለል እንደሚታዎቀው አሻጥራቸዉም ተሳካላቸዉና ቅንጅትም ፈረሰ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጽም ተበልቶ ልጆቹም ተገድለው ተጠናቀቀ።

  ትንሽ ቆይተው በፈረንጁ ሐገር ተጠልሎ የሚኖረውን ሐገር ወዳድ ሕዝብ በመከራ ለፍቶ ሰርቶ ያፈራትን ገንዘቡን ተረከቡት፤ ዘረፉት ማለቱ ይቀላል። ግንቦት 7 የሚባል ድርጅት አቁቋመናል “በስድስት ወር ነጻ ልናወጣህ ነውና የአርበኝነት 500 ዶላር አዋጣ” እያሉ እሾህ ከሌለበት ዛፍ እንደ ወጣ ፍሬ በሽሚያ ሸመጠጡት። እኛም ቀዝቀዝ በሉ እነዚህ ከወያኔ ጋር የሚሰሩ ጠላቶች ናቸዉ ብንል ማን ይስማን? ድምጻችን የቁራ ድምጽ ሆነ። ግን፤ ግን እዉነት አትጠፋምና እንኳን በስድስት ወር ነጻነት ሊያመጡ ይ ቅርና ለአመታት እየተቁለጨለጩ ተመላልሰው በሉ። ምክንያቱም ሰዎቹ አላማቸው ኢትዮጲያን ማዳን ሳይሆን የወያኔን እድሜ ለማስረዘም የተቀጠሩ ቅጥረኞች ስለሆኑ ነበር።

  የስልክ ወታደሮች፤ አየር በአየር ተዋጊዎችና የአስመራ አባ ሻዎል ጄኔራሎች

  በጎንደርና በጎጃም ገበሬው መነቃነቅ ሲጀምር በሌላ መንገድ ተዘጋጅተው “አማራዉ ከተነሳ” ነገር ተበላሸ ደሞዝ ከፋያችን ወያኔም አለቀላት ብለው አማራዉን እንዲዘናጋ የማስመሰያ ጦር ሰራዊት መሰረትን አሉ (ሰራዊታችዉን ያየ የለምና አሉ ማለት ይቀላል)። ከዚህ ላይ አንባቢያን እንዲረዱት የምፈልገዉና ብዙው ሰው ያልተረዳው ነገር ቢኖር፤ ግንቦት 7 ጦር ኖሮት አያ ዉቅም፤ ማንን ሊወጋ? ደሞዝ ከፋዩን ወያኔን? የማይሆን ነገር ስለነበር ተዋግቶም አያዉቅም። ታዲያ ጦር አለኝ እንዲል ያስገደደው ምን ነበር? ብሎ ለሚጠይቅ መልሱ ቀላል ነው። አሁንም ልድገመዉና የአማራ ገበሬዎች ጦር መሳሪያ አንስተው እየተዋጉ እንዳይቀጥሉ እኛ አለን፤ ለእኛ ተዉት ብሎ ለማዘናጋትና ተቃዉሞውን አለዝበው ለወያኔ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር አማራዉን እንዲፈጅ ለማመቻቸት ብቻ ነው። በዚህም እራሳቸው ተጠቅመው ወያኔንም ጠቅመዋል። አሁንም እንደገና እነርሱ አስመራ ቢራ እየጠጡ አርበኞቻችን በጎንደ ር እየተዋጉ ነው እያሉ ከወያኔ ጋር እየተነጋገሩ የአማራዉን ወጣት እያሳፈሱ እስር ቤት አስጨመሩ፤ አስገረፉ፤ አስደበድቡ ና አስገደሉ። ያው ከላይ እንደገለጽኩት አንዳርጋቸው ጽጌ ከዉጭ፤ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከዉስጥ ሆነው ቅንጅትን ለማፍረስ ይሰሩ እ ንደበሩት አሻጥር ማለት ነው።

  በዚህኛው ዙር ግን ግንቦት 7 ከዉጭ(አስመራ) ወያኔ ከዉስጥ(አዲስ አበባ) ሆነዉ ነበር ድራማው የተካ ሄደው። ከዚያም አልፎ ነገሩ ሳይረዳቸው ድርጅት ያለ መስሏቸው ብዙ የአማራ ልጆች በመታለል ኤርትራ ከደረሱ በኋላ ግንቦት 7 የዉሸ ት ድርጅት መሆኑን ስላወቁ ብቻ በግንቦት 7 መሪወች ትእዛዝ ምስጢር እንዳያወጡ እየተባለ በኤርትራ ምድር በየመንገዱ ተረሽነዋል። ለዚህም ከግንቦት 7 ጋር ያበሩት የኤርትራን ተባባሪዎችም ጊዜው ሲደርስ የሚያስጠይቃቸው ይመስለኛል። ታሪክም መዝግቦት የሚቆይ እና የእ ነዚያ የአማራ ወጣቶች ደም ከንቱ ሆኖ የሚቀርም አይደለም። ቀጠሉና ከኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ጋር ግንባር ፈጠርን አሉን። የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር የተፈጠረው ቀደም ብሎ ግንቦቴዎቹ ከመፈጠራቸው በፊት ነው። ነፍሱን ይማረዉና ቅጣው እጅ ጉም እንደዚሁ የአርበኞችን ስም የያዘ ድርጂት አቋቁሞ ነበር። ኢትዮጵያ ከሚለው ጋር ጸብ ያላቸው እነግንቦት 7 ግን ይህንንም ማፍረ ስ ነበረባቸው። አስመራ የነበሩትን ጥቂት አርበኞች በግዳጅ ከሻቢያ ጋር ይዘው አርበኞች ግንቦት 7 መሰረትን ተባለና ወዲያዉኑ ኢ ትዮጵያ የሚለዉን ስም ፋቁ። ቀጥለዉም ጥቂት የአርበኞቹን አባሎችም ግማሹን ለሻእብያ ነግረው በማሳሰር፤ የቀሩትንም ጥለው እንዲዎጡ በ ማድረግ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርን አፈረሱና አርበኞች ግንቦት 7 ነን ብለው ብቅ አሉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ በትጥቅ ትግል የተሰማሩት የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርም በነገሩ በመገረም ግንቦት ሰባትን በመወረፍ ስማችን ቀሙን እኛም ግንቦት 7 ከሚባል ጋ ር ግንባር የለንም ለብቻችን ነው እያሉ በመግለጫቸው ደጋግመው ሲነግሩን ቆይተዋል። ሆኖም የኢሳት ባለቤት የሆነው ግንቦት 7 ግን ድርቅ በማለት የሌለዉን አርበኞች ግንቦት 7 እያለ እስካሁን ይዋሻል። ግንቦት 7 እና ሜዲያው ኢሳት በሬ ወለደ እያሉ ያልተ ሰራዉን ተሰራ፤ ያልፈጸሙትን ጀብድ ሰራነ እያሉ ወሬያቸዉን ሲቀጥሉ ዉሸት የሚያጋልጡትን ደግሞ አፈኑ። ዉርደታቸው ግን እየጨመ ረ እንጅ እየቀነሰ አልሄደም። ከዴምህትና ከኦነግም ጋር ግንባር ፈጠርን አሉን። ኢሳትም እንዳለ የብሄር አለቆቹን በተራ እያቀረበ አስተዋዎቀን ለአማራዎች ግን አንድም እድል አልሰጡም። ኢሳት የአማራው ድምጽ እንዳይሰማ ከሚያደርጉት ዋናው ተዋናኝ ነበር ማለት ይቻላል። የተገንጣይ መሪዎቹን በየተራ እያመጣ መርዝ ሲያስተፋብን በተመሳሳይ ጊዜ ግን ከሰባ ሽህ በላይ በነሽ ፈራው ሽጉጤ ትእዛዝ ተዘርፈዉና ተደብድበው የተባረሩትን አማሮች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማሳየት ተጠየፏቸው። ከብዙ ጩኸት በኋላ ነው ትንሽ ብ ቅ ያደረጓቸው። ቆይተዉም ከትግራይ አኩራፊዎችም ከኦነግም ጋር ግንባር ፈጠርን ባሉን ጥቂት ወራት ዉስጥ የትግሬዎች ሽፍታ ሞላ አስገዶም የስለላ ስራዉን ጨርሶ ወደ ኢትዮጵያ ገባ። የግንቦት 7 ጉድ በዚህም ሳያበቃ ቆይቶ ኦነግም ደህና ሁኑ ሳይ ላቸው ኢትዮጵያ ገብቷል።

  እነርሱ  ግን በአማራና በኢትዮጵያዊነት ያላቸዉን አመለካከት ለመቀየር ፍንክች አላሉም። የእንጀራ ነገር ስለሆነባቸው ጠላታቸውም አማራ ሆኖ ገንዘብም የሚሰበስቡት አሻጥሩን ካልተረዱት ከአማራው ልጆች ነበር። ከዚህ ላይ እኔ ኢሳት ዉስጥ ከሚሰሩት ጋዜጠ ኞች ጋር ጸብ የለኝም፤ የሚሰሩት ተቀጥረው ነው የሚከፍላቸዉ ከግብጽም ያምጣው ከኤርትራ ያው ግንቦት 7 የሚባለው ጉ ድ ነው። ስለዚህም የእንጀራ ነገር ስለሆነ የሰሩትን እየሰሩ ነው። ቢሆንም እንዲያው ለተመልካች እንኳን አማራዎችን ደብ ለቅ በማድረግ ብሶታቸዉን ሕዝብ እንዲሰማው ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር። ግን አላደረጉትም። አንድ ጊዜ አቶ ተክሌ የሻዉን ለማሟያ ቢያቀርቡትም የአማራ ተቆርቋሪነቱ ስለጠነከረባቸው ከእርሱ ወዲያ እርም ነው ያሉ መሰለኝ የአማራና የኢሳት ነገር በዚህ ተጥናቀቀ እንበልና እንተወው።

  በሌላው በኩል ግን ቀጠሉ ግንቦት 7 ጀብድ ሰራ፤ በዚህ ገደለ በዚህ ገባ፤ወጣ እያሉ ህዝ ቡን አደናገሩት። የጎንደር ገበሬዎች ከወያኔ ጋር ገጥመው ጥይት ሲተኩሱ፤ እኛ ነን የተኮስነው ማለት ጀመሩ። እንዲያዉም አንድ ጊዜ አንድ ሻለቃ ጦር መጥቶ ተ ቀላቀለን ብለው ከወያኔ የተላከላቸዉን የወታደሮች ፎቶ በቴሌቪዥን አሳዩን፤ እኛም ይሁን እናያለን ብለን ጠበቅን። እ ነርሱም የስልክ ወታደር ገንዘብ እየከፈሉ ቀጠሩ። የስልክ ወታደር የማያዉቅ ካለ ነገሩ እንዲህ ነዉ። ግንቦት 7 በየከተማው በተለይም ጎንደርና ጎጃም ዉስጥ ባሉ ቦታዎች ገንዘብ እየከፈላቸው ስልክ የሚደዉሉ ሰራተኞች ናቸው። እነዚህ ስልክ ደዋዮች፤ ገበሬዎቹ ከወያኔ ጋር በገጠሙ ቀን ወሬ ፈልገው ለግንቦት 7 ወይም ለኢሳት ደዉለው እንዲህ አደረግን የሚሉ ናቸው። አንዳንድ የሚያስቁ ገጠመኞችም ነበሩ፡ እነዚህ የግንቦት 7 ስልክ ደዋዮቹ አንዳንዴ ስራ ከምንፈታ እያሉ ነው መሰል (እንጀራ አይደል) ከጎንደር ከተማ አስር ኪሎ ሜትር ከማይርቅ ቦታ በወያኔ ወታደር ላይ ግንቦት 7 ጥቃት አደረሰ እያሉ ሲዋሹ፤ ኢሳትም ያን ዉሸት እየተቀበለ ሲያነበንብ፤ የአካባ ቢው ሕዝብ ካዳመጠ በኋላ ነገሩን ማገናዘብ ጀመረ። ነገሩ እየተበላሸ የሄደው ጥቃት ካልደረሰበት ግን ጥቃት ደርሷል እየተባለ ከሚወራለት ቦታ አካባቢ ያለው ሕዝብ በመደናገሩ ግንቦት 7 ለመሆኑ ማነው? ለምንድን ነው ይህን ያህል ዉሸት እየዋሸ እኛን የሚ ያታልለን ማለት የጀመረ ጊዜ ነው(አሁንስ አሻጥሩ የተጠማዘዘ ስለሆነ ለመግለጽም ተቸገርኩ)። የግንቦቴዎቹ ነገር “የማይነጋ መስሎሽ....” ሆነና ለሕዝቡ እየተገለጸለት መጣ። ጎንደር ከከተማዉ ደ መቀ ዘዉዱ የወያኔን አፋኝ ቡድን ለመከላከል ሲታኮስ ሕዝቡም ወጥቶ በንዴት ተቀላቀለውና እራሱን መከላከል ሲጀምር አንድ ትልቅ ጥያቄ ተነሳ። ይህ ጥያቄ ተድበስብሶ ወይም ተመካኝቶ የሚያልፍ አልነበረም። ግንቦት 7 የት አለ? ተባለ። ግንቦት 7 ወሬዉም ድራሹም ጠ ፋ። ይህ ሲሆን ከድሮዉም አለመኖሩን የምናዉቀው መጋለጡ ደስ ሲለን፤ ያልጠበቁት ዉሸት ከፊታቸው የተደቀነባቸው ጎንደሬዎች ግን ተናደዱ፤ ግንቦት 7 ማን እንደሆነም አዎቁ። የኢሳት ጋዜጠኞች እስኪያፍሩ ድረስ፤ ግንቦት 7 የት ነው ያለው? እየተባሉ በ ጎንደሬዎች ጥያቄ ተዋከቡ። ምኑን ይመልሱት፤ ዶ/ር ብርሃኑም ዝም፤ ነአምን ዘለቀም ዝም፤ ሁሉም ዝም፤ የሌለዉን ከየት ይ ምጣ? ቄሱም፤ መጽሃፉም ዝም ሆኑና አረፉት። ከዚያ ተማከሩ መሰለኝ በሁለተኛው ሳምንት በቴሌቪዥን መስኮት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ብቅ ብሎ "ይህ የእኛ ትግል አይደለም የሕዝቡ ትግል ነዉ" ብሎ እቅጩን ነግሮን መልሶ ተሰወረ።

  ይህን ስንሰማ የግንቦት 7ን ሸፍጥ ለምናዉቀው የነገረን ትክክል ስለሆነ አላስደነቀንም። ድሮም ይሁን አሁንም የሕዝብ ትግል እንጅ ግንቦት 7 የሚባል አጭበርባሪ ቡድን ምንም የማ ያደርግ አስመሳይ አዘናጊ ቡድን መሆኑን ሕዝቡ አረጋገጠ። ጎንደሮችም ሆኑ በጠቅላላ አማራዎች ያችን እለት ነበር ብቻ ቸዉን የጀመሩትን መጨርስ እንዳለባቸው የተረዳቸዉ። በዚያች የሃምሌ ወር የጎንደሮች መነሳት ለወያኔም ሆነ ለግንቦት 7 ወደ መቃ ብራቸው እንዲሄዱ መንገድ የተጠረገበት ቀን ነበር ብለን በሙሉ እምነት መናገር ችለናል።

  በቅርቡ ደግሞ ወልዲያ ላይ የትግ ሬ ወያኔዎች የጥምቀት በዓል በሚያከብሩ አማራዎች ላይ ታቦት እስኪወድቅ ድረስ ጥይት እያርከፈከፉ ከህፃን እስክ ሽማግሌ ሲ ጨፈጭፉ፤ ሌላዉም ድርጊቱን ሲያዎግዝ ነዉር የማያዉቀው ግንቦት 7 ያወጣው መግለጫ ግን ምንም ያልሆኑትን ትግሬዎች ተበደሉ ብሎ ነ በር። ከዚህ በላይ የአማራ ጥላቻ ይኖር ይሆን? ለአማራ ጠላትነት ግንቦት 7 ከወያኔ የበለጠ እንጅ ያነሰ አይደለም። አማራዉን ማግለልና በስሙ መነገድ የግንቦት 7 ዋና መመሪያዉ ነው።

  ግንቦት 7 ዉስጥ አማራ የሚባል የአመራር አባል የለም። ከእኛ በላይ ወገኑን አዋቂ ሊመጣ ስለማይችል፤ አለ ካለ ይንገረንና ማን እንደሆነ እንነግረዋለን። እንዲያዉም በፕሮግራሙ አስፍሮታል “ሁለት ቋንቋ የማይናገር ከአመራር መግባት አይችልም” ብሎ አስቀምጧል። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? የጠራ አማራ የግንቦት 7 አመራር መሆን አይፈቀድለትም ማለት ነው ። ግን ወታደር ሆኖ እነ ብርሃኑንና አንዳርጋቸዉን ከስልጣን በደሙ ከፍሎ እንዲያደርስ ይፈቀድለታል ማለት ነው። ተግባባን! ግንቦት 7 ሊሰራ የሚፈልገዉም፤ የሚያስበዉም፤ የሚያልመዉም ጸረ አማራ አፈጣጠር ካላቸው ድርጅቶች ጋር ብቻ ነው። የተፈጠረዉም ለዚሁ አላማ እንደሆነ ከላይ የዘረዘርኳቸው በቂ ምስክሮች ናቸው።

  ግንቦቴዎቹ የሚመሩት ጥርቅሞች ከአማራ ህብረተሰብ አንዳቸዉም ያልተፈጠሩ ያለጦር ሰራዊት ጦር ሜዳ ዉለናል የሚሉ፤ አየር በአየር በምላሳቸዉ ብቻ የሚዋጉና አስመራ አባ ሻዎል ዉስጥ የኖሩ የቡና ቤት ጀ ኔራሎች ናቸው። ይህ የማይረዳው አማራ ካለ ጭንቅላቱን መመርመር ያስፈልገዋል። አሁን ደግሞ ጦር የሌለው ባለጦሩ ግንቦት 7 ትግል ላይ ያልነበሩትን ታጋዮቹን በክብር ሸኝቻለሁ ካለን በኋላ በዘረፈው ገንዘብ አዲስ አበባ ላይ ልገባ ነኝና ደ ግሱልኝ በማለት ቀጥሮ እያስደገሰ ነው። እነዚያ ትንታግ ወጣት ፋኖዎች ካሉበት ጎንደርና ባህርዳር እንኳን ግንቦት 7 ትርው የሚል አይመስለኝም። ለ ሁሉም የአማራ ልጆች የሆናችሁ ሁሉ ከእነዚህ አጭበርባሪ ቡድኖች ግብዣ ብትገኙ በግፍ የተገደሉትን የወንድም እህቶቻችሁን ስጋና ደም እንደበላችሁ ይቆጠራል።

  ኢትዮጵያ ሐገራችን ለዘላለም ትኑር

  ጋሻው ቀለሙ

  « Back to archive
 • Leave your comment

 • Name:
   
  Email:
  Comment   
  captcha
  Enter the code shown above: