• News

 • በኢንጂነር ስመኘው ላይ ፖሊስ ያቀረበው የምርመራ ውጤት አነጋጋሪ ሆኗል። 07 September 2018 | View comments

 • በኢንጂነር ስመኘው ላይ ፖሊስ ያቀረበው የምርመራ ውጤት አነጋጋሪ ሆኗል።

  ፖሊስ ኢንጂነሩ ራሳቸውን ገደሉ ያለው በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት አጥቷል። ፖሊስ ይህን ያህል ጊዜ ዘግይቶ እንዲሁም የምርመራውን ውጤት አስመልክቶ ሁለት ጊዜ መግለጫውን መሰረዙ ጥርጣሬን ከማሳደሩም በላይ ውጤቱ ሃሰተና ነው በሚለውው በርካቶች ይስማማሉ።

  ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ራሳቸውን ማጥፋታቸውን የፖሊስ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

  የምርመራ ቡድኑ እንዳስታወቀው ሞተው የተገኙበት መኪና ውስጥ የተገኘው ሽጉጥም በእርሳቸው ስም ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ተመዝግቦ የሚገኝ ነው።

  በፎረንሲክ ምርመራ በተገኘው ውጤት መሰረትም የሽጉጡ ቀልሃና የተገኘው እርሳስም የዚሁ ሽጉጥ መሆኑን ፖሊስ እንዳረጋገጠ አስታውቋል።

  ኢንጅነር ስመኘው ከመሞታቸው ቀደም ብሎ ባሉት ቀንም ሆነ በዕለቱ ጠዋት ያደረጓቸው የስልክ ልውውጦችም ሆነ የፖስታ መልዕክቶች የስንብት ይዘት ያለቸው መሆኑንም በመግለጫው ተጠቁሟል።

   

  በመጨረሻም እንደተጠበቀው ኢንጂነሩ
  ራሱን አጠፍቷል ተብሏል
  *★★★*

  ~ "ትናንት ኢትዮጵያ ላይ ኢንጅነር ስመኘው የተባለ ሠው ለሀገሩ እየሠራ እያለ #በአደባባይ_ተገድሏል! በአደባባይ
  ሠው የሚገደልበት ሀገር እንደመምራት አሳፋሪ ነገር የለም" ጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድ በአሜሪካ ሳሉ የሰጡት ምስክርነት።

  ~ የለም የለም ኢንጅነር ስመኘው ራሱን ነው ያጠፋው። ኮሚሽነር ዘይኑ ዛሬ በሰጡት ይፋዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት።

  #ETHIOPIA | ~ Zemede ትላለች በሀገረ እንጊሊዝ የምትኖር መሰረት በየነ የተባለች እህቴ ኢንጅነር ስመኘው ፣ እራሱ ገደለ ካልን ፦

  1. በግራ በኩል ጆሮው ላይ ተተኩሶበት ሽጉጡ ለምን በቀኝ እጁ ላይ ተገኘ?

  2. እራሱን ያጠፋ ሰው ሽጉጥ እንደጨበጠ ለመሞትስ አቅም ይኖረዋልን? ከእጁ ላይ ይወድቅበታል እንጂ በማለት ትጠይቃለች።

  ራሱን በሽጉጥ ያጠፋ ሰው አይፈራገጥም ወይ? ደሙስ አካባቢውን አይበክልም ወይ፣ እንዴት ኮፍያውን እንዳደረገ፣ ፎቶ እንደሚነሳ ሰው ወንበር ላይ ተስተካክሎ ይቀመጣል? ጥያቄዎች ከዚህም ከዚያም ይቀጥላሉ። መንግሥት ግን አሰብና ምጽዋን እንድንጠቀምበት ተደራድሬላችኋለሁ። ሜቴክ ገንዘቡን በልቶታል። ግን አይጠየቁም፣ አይከሰሱም፣ እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው። ሁለተኛ ገንዘብ ያለበት ቦታ አናደርሳቸውም እያለ እያስቀየሰን ነው የሚሉም አሉ። ለማንኛውም ፦

  ~አንዳንድ ሰዎች ሁለት ጊዜ ይሞታሉ።
  .
  .
  .

  በመጀመሪያው በግፍ ይገደላሉ።
  .
  .
  .

  ሁለተኛው ሞት ደግሞ ከሞቱም በኋላ ለግፍ ግድያው ራሳቸው ኃላፊነቱን እንዲወስዱ ይደረጋሉ።
  .
  .
  .

  እናም በግፍ የሚገደሉ ታላላቅ ሰዎች፣ ብዙ ጊዜ ሁለቴ ነው የሚሞቱት።
  .
  .
  .

  ኢንጅነሩም ሁለት ጊዜ ተገደሉ ማለት ነው። [ አስተያየት ሰጪ ]።
  .
  .
  .
  77 ቢልየን የስኳር ብር አጣጥመው በሉ የሚባሉ ግለሰቦች ምንም ሳይሳቀቁ በሰላም ተንደላቅቀው በሚኖሩባት ኢትዮጵያ፤ ምስኪኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ከልጆቹ ጉረሮ ቀንሶ ለግድቡ ያዋጣውን ብር ቀርጥፈው የበሉ ግለሰቦች ውስኪ እየተራጩ ዘና ፈታ ብለው በሚኖሩበት ሀገር፤ እንዴት አንድ ከገንዘብ ጋር ንክኪ ሳይኖረው በሙያው ብቻ ከብረትና ከአሸዋ፣ ከድንጋይና ከበረሃ ሙቀት ጋር ሲታገል የሚውልና የሚያድር ምስኪን ሰው ራሱን አጠፋ ይባላል ?

  ~ እናም እኔ ግን እላለሁ፤ ሁሉን አዋቂው፤ አድልዎ መድልዎ የማያቀው። ትክክለኛ ፍርድ የባህሪ ገንዘቡ የሆነው እውነተኛው ፈራጅ ልዑል እግዚአብሔር ትክክለኛውን ፍርድ ይስጥ።

  ሻሎም ! ሰላም !

  ዘመድኩን በቀለ ነኝ ።
  ጳጉሜ 2 /2010 ዓም
  ከራየን ወንዝ ዳር።

  Source: https://en-gb.facebook.com/ZemedkunBekeleB/

  « Back to archive
 • Leave your comment

 • Name:
   
  Email:
  Comment   
  captcha
  Enter the code shown above: