• News

 • ታማኝ በየነ --- መጥምቁ ዮሃንስ --- ሊመጣ ላለው መንገድ ጠራጊ 10 September 2018 | View comments

 • ታማኝ በየነ --- መጥምቁ ዮሃንስ --- ሊመጣ ላለው መንገድ ጠራጊ

  የሰሞኑ የታምኝ በየነ ወደኢትዮጵያ ጉዞ ከአንድ በላይ ተልእኮ እንደነበረው የገባኝ እሱ ሃገር ቤት ገብቶ በአማራው ክልል በቀበጣጠረው ቅብጥርጥሮሽና መሰሪ ተግባሮቹ ነበር። መቼም እንደማንኛውም ሃገሩን እንደሚናፍቅ ዜጋ ከ 22 አመታት ቆይታ በሁዋላ ቤተሰቡንና ምድሪቱን ለማየ ት የተከሰተውን ነፃነት ቢጤ ተጠቅሞ ወደ ውድ ሃገሩ መሄዱ የመጀመሪያውና ማንም የገመተው ምክንያቱ ነበር። ታማኝ ኢትዮጵያን እንደሚወድ ማንም የመሰከረለት ሃቅ ነው። ከባለቤቱ ከፋንቱሽ ጋር ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጀምሮ በረገጠበት በእያንዳንዱ ስንዝር መሬት ለአፄዎቹ እንኩዋን ባልተዘከረ መዘክር ነበር ህዝቡ ያንቆለጳጰሰው። መሲህ እንደመጣ አይነት። በሚሊኒየም አዳራሽ ያደረገው ንግግር ስለአንድነትና ስለመስ ዋእትነት ብሎም ስለወደፊቱ ትግል እነጃዋርንም እንተባበር በሚል መልኩ ያካተተ ስለነበር እስከዛች ሰአት ድረስ የታማኝን ሁለተኛ እጀንዳ የሚያሳብቅ ምንም ነገር አልታየበትም። ኦሮሞውንም አማራውንም ሌሎቹንም ብሄሮች ለለውጡ ዘብ እንቁም ብሎ የጠየቀበት ጤናማ ንግግር ነበር።

  በሁዋላም ጉዞ ወደባህር ዳርና ወደ ጎንደር ወደ ደብረታቦር ሆነና ታማኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሜሪካ የመጣበትን ሁለተኛውን እጀንዳውን ከቁዋ ጠሮው ፈታ። ታማኝ በአማራው ክልል ከእናት ሃገር ጥሪው በተጉዋዳኝ እየፈራና እየተባ ታላቁን የአማራ ህዝብ ስለኢትዮጵያዊነት መስበክ ጀመረ። በአንድ ወቅት በባህርዳር ይመስለኛል አማራውን ህዝብ “ እናንተ ክልል የሚባል ነገር አይገድባችሁም ኢትዮጵያ ሁሉ የእናንተ ነው ” ሲል፣ ይህ ሰው ምን ማለቱ ነው ? ሃገሪቱ በክልል ተከፋፍላ ስትተዳደር 27 አመታት አለፋት። ኦሮሞም ክልሉን፣ ትግሬም ክልሉን፣ ደቡብም ክልሉ ን ወዘተ በተናካሽ ውሾች እያስጠበቀ ባለበት በዚህ ዘመን አማራውን ከዚችው ከተረፈችው የተቆራረሰች ክልሉም ሳይሆን ተንከራታች እንዲሆን የእብድ ምክር መምከሩ በውስጤ የመርዝ ያህል ነበር ያናወጥኝ።

  “ ክልል አያግዳችሁም ” ብሎ የተናገራቸው አማሮች ምንተ እፍረታቸውን ቢያጨበጭቡም “ ምን ለማለት ፈልጎ ነው ” በሚል ጥያቄ ሳይሞሉ አልቀሩም። አማሮች እኛ ክልል አይገድበንም ብለው ስላሉ በክልል መገደባቸው ሊቀር ነው ? አይ ቀልድ !!! እንዲያውም ስለ ክልል ካነሳን አይቀር ለመሆኑ ማነው የአማራውን ያህል በክልሉ እንዲገደብ የተደረገ ? አማራው ወደ ክልልህ ጥፋ ያልተባለበት የኢትዮጵያ ግዛት አለ እንዴ ? ያው የራሱ ክልል ካልሆነ በተቀር ? ታማኝ መጃጃሉ ነው ወይስ አማራውን በገሃድ ለማሞኘቱ መሞከሩ ? ሌላው ቢቀር አማራው በክልሉ የተገደበና በማንነቱ የተወገዘ ብሄር መሆኑን ያጣዋልና ነው ታማኝ እናንተ በክልል የተ ገደባችሁ መሆን የለባችሁም ብሎ በቁስላቸው ላይ እንጨት የሚሰድበት ? እውነታውንና በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ እንደመተሬ እየመረረው ለተጋተ ህዝብ ይህን የመሰለ ባዶ ቅስቀሳ ማድረግ ምን ይሉታል ? ነው ወይስ ታማኛችን ሌላ አጀንዳ ነበረው ?

  የታማኝ ሁለተኛ የሃገር ቤት ጉዞ ተልእኮው ገሃድ የወጣበት ወልቃይት ጠገዴ የኢትዮጵያ ነው ብሎ በመናገር በታላቁ አማራ ህዝብ ፊት ወጥ የረገጠበት አጋጣሚ ነ በር። ህዝቡ ይህንን የግንቦት 7 ቶች ተረት ከታማኝ አንደበት እንደሰማ ሳያመነታ በጩሀት “ የአማራ ነው ” “ የአማራ ነው ” ብሎ ሲያቡዋርቅበት የግንቦት 7 ቱ መንገድ ጠራጊ ታማኝ የንብ ቀፎ እንደነካ ወዲያው ታወቀው። “ አስጨርሱኛ ” ብሎ ከተማፀነ በሁዋላም ይዘላብድ ጀመር። ከተጠበቀውም በላይ የተቆጣውን ህዝብ ለማባበል እሱ ( ታማኝ ) የአማራው አጋር እንደ ሆነ የሚያሳዩ ዝክሮችን አነበነበ። ታማኝ አማራውን ብዙ ተዳፍሮት ነበር የከረመው። በብሄሩ ፍዳውን ያየውን የአማራን ህዝብ ኦሮሞው ፣ ትግሬው፣ አፋሩ፣ ሲዳማው፣ በኒሻንጉሉ፣ ወዘተ በብሄር ተደራጅተው የህዝባቸውን ጥቅም ለማስከበርና በወደፊቱዋ ኢትዮጵያ ያላቸውን ድርሻ ለማረጋገጥ በሚራወጡበት በዚህ ዘመን አማራውን በብሄሩ ሳይደራጅ እንደተዝረከረከ የሌሎች ስልጣን መወጣጫ ሆኖም እንዲቀር መርዙን ሊረጭ ሞክሮአል። እንድ ወጣት ታማኝ በተገኘበት በአንድ ስብሰባ ላ ይ ታማኝን የክልሉ ተወላጅ እንደመሆንህ አማራው በብሄር እንዲደራጅ ማበረታታ የነበረብህ አንተ ልትሆን በተገባ ነበር ብሎ ሲናገር የተጠቀመው ቃል “ እንዲያውም ፊት አውራሪያችን ” መሆን ነበረብህ የሚል ነበር። ሰው የገዛ ብሄሩን ለሌሎች፣ ለዚያውም 2 ለብሄሩ ጠላቶች ስልጣን መቆናጠጫ ጀሌ ለማድረግ ከመሮጥ የበለጠ የባንዳነት ባንዳ አለ ቢሉኝ በአይኔ በብረቱ እስከማይ አላምንም። እንግዲህ ታማኝ ወደ ሃገሩ የተመለ ሰበት ምክንያት አንደኛው የናፈቀውን ምድርና ህዝብ ለማየት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የግንቦት 7 ቶች መንገድ ጠራጊ ለመሆን ነበር።

  መጥምቁ ዮሃንስ ለኢየሱስ መንገድ ሲጠርግለት እኔ በውሃ አጠመቅሁዋችሁ ነገር ግን ከእኔ የበለጠ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቃችሁ ይመጣልና ተዘጋጁለት ብሎ እንዳለው፣ ታማኝም ከግንቦት 7 ቶች ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ አስቀድሞ በመሄድ አማራውን በባዶ የአንድነትና የኢትዮጵያዊነት ቅፈላ ብሄር ተኝነቱን አስጥሎ ለአጭበርባሪው የአማራ ጠላት ግንቦት 7 ሆ ብሎ እንዲገብር የማድረግ ተልእኮ ነበር ያነገበው።

  ወንድማችን ታማኝ ለአማራው ቀንደኛ ጠላት ለግንቦት 7 እቡይ ( እኩይ ) አላማ አስፋልት አነጣፊና የጦር አዝማች ሆኖ የገዛ ብሄሩን ሊሽጥ የተነሳሳበትን ምክንያት ምን ይሆን ብዬ ስጠይቅ አንዳንድ ምክንያቶች ወደ አእምሮዬ ይመጣሉ። ታማኝ የኢሳትና የግንቦት 7 አካል ነው። በደሞዝም እንደሚያስተዳድሩ ት እውቅ ነው። እዚህ ላይ በእርግጠኝነት ከኢሳት ደሞዝ እንደሚከፈለው መናገር ይቻላል። ኢሳት ደግሞ የግንቦት 7 ንብረት ነው። በነገራችን ላይ ኢሳት የህዝብ ነው የሚለውን የሞኞች ጨዋታ ማንም የሚጫወተው ሊኖር አይገባም። ታማኝ በብሄር መደራጀትን ሲቃወም የአማራው በብሄር መደራጀት ከነ ኦነግና ከ ቲ ፒ ኤል ኤፍ ወይም ከኦጋዴን ነፃ አውጭ ወይም ከሲዳማ ብሄር ንቅናቄ ጋር በአላማው አንድ እንዳልሆነ አጥቶት አይመስለኝም። ያንን ያልተረዳ ከሆነ የአእምሮ ዝግምተኛ ነው እላለሁ። አማራው በብሄር እንዳይደራጅ የሚጮሁት እነአንዳርጋቸው ፅጌና እነብርሃኑ ነጋም ጭምር የአማራው በብሄር መደራጀት ለኢትዮጵያ አንድነት አስፈላጊ እንደሆን አጥተውት አይደለም። እንዲያው በብሄሩ የተደራጀና የታጠቀ አማራ ከኦሮሞዎች ለሚመጣው የስልጣን ይገባናል ፉከራ ማቻቻያ (balance of power) ብቸኛውና አማራጭ የማይገኝለት ነገር እንደሆን ያውቁታል።

  ታዲያ ለምን ይሆን ለኢትዮጵያ አንድነት ቆመናል የሚሉት እነኝህ የፖሊቲካ ዱር አዳሪዎች አማራው በብሄሩ ተደራጅቶ የራሱ ድምፅ እንዳይኖረው የሚታገሉት ???? ስልጣን ! ስልጣን ! ስልጣን ! ። አማራው በብሄሩ ከተደራጀ ግንቦት 7 ከኦሮሞዎች ጋር ለስልጣን ለመፎካከር የሚያስችለው የድምፅ ወይም የአባል ቁጥር አይኖረውም። አማራውን ከአማራነቱ መነጠልና ከኢትዮጵያዊነት መረሆ ጋር አደንዝዞ ለብርሃ ኑ ነጋና ለአንዳርጋቸው ፅጌ የቤተ መንግስት ንግስና አብሳሪ እንዲሆን ማድረግ ነው የግንቦት 7 እቅዱና አላማው። ለዚህም ነበር ታማኝ በየነ በብሄር አትደራጁ የሚለውን መፈክሩን ይዞ ለግንቦቴዎችመንገድ ሊጠርግ ቀደም ብሎ ወደ አማራው ክልል የነጎደው። ኢትዮጵያ የሄደበትም ጊዜ በአጋጣሚ የሆነ አልመሰለኝም። ግንቦት 7 ቶች ወደ ሃገር ቤት ከመሄዳቸው በፊት ታማኝን የማስቀደሙ ፕላን የተመከረበትና የተዘከረበት ጉዳይ ነው ብዬ አምናለሁ። አማራው ክልልም ከደረሰ በሁዋላ በምን ጉዳዮች ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለበት የተዶለተበት ጉዳይ ነው ብዬ አምናለሁ። የእንጀራው ጌቶች ናቸውና ትእዛዛቸውን ይዞ ነበር የሄደው ማለት እደፍራለሁ።

  የአማራውስ መጃጃል ለመሆኑ በጤናው ነው ?

  ታማኝን ለመቀበል የተደረገው ዝግጅት ለዶ / ር አቢይ ከተደረገው ድጋፍና ትእይንት ቢያንስ በጥቂት ነው። አይ ወገኔ !!

  ክልሌ አማራ ሞኝ ነሽ ተላላ

  የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ

  ለመሆኑ ምነው የአማራን ማንነት ክብር ብቻውን ታግሎ በዳያስፖራው መሃል ያለመለመውን ታላቁን ተክሌ የሻውን እንደ ታማኝ በአደባባይ አልዘከሩትም ??? ተክሌ የሻው በእኔ ግምት ከአፄዎቹ የማይተናነስ ተጋድሎ ያደረገ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። ታሪክም ትልቅ ስፍራ እንደሚሰጠው እምናለሁ። የተክሌ 3 የሻው ሃገርቤት መግባትም በሚዲያውም በቅጡ አልተሸፈነም ። እነደመቀ መኮንን እንደተቀበሉት አውቃለሁ። ነገር ግን በእኔ ግምት ያ በቂ አልነበረም ለዚህ የአማራ ጀግና። እንግዲያውማ ለአማራው የሞተው ተክሌ አልነበር ? ተክሌ ታማኝ በየነ አባል በሆነበት በኢሳት ኢንተርቪው እየተጋበዘ እነ ፋሲል የኔ አለም ( ሌላው አማራና የአማራ ጠላት ) ሊያዋርዱት ሲሞክሩና ሲያብጠለጥሉት በተደጋጋሚ ተከታትያለሁ። በዳያስፖራ ያለው አማራ በአማራነቱ ተሽማቆ ብሄሩን ሲክድ በነበረበት ቅውጢ ጊዜ ጀግናው ተክሌ የሻው አማራ ነኝ፣ አማራን በሃስት አተወንጅሉ፣ ብሎ በእውቀትና በጥበብ ተነሳ። ተክሌን መጀመሪያ የተቃወመው አማራው ራሱ ነበር። ስንቱን አለፈው ተክሌ በአማራነቱ ?? ግንቦቴዎች ተክሌ የሻውን በጉባኤያቸውም ሆነ በህብረታቸው ላይጋብዙት ተማምለዋል ምክንያቱም ተክሌ የአማራውንና የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የማይሸጥ ግትር አማራ በመሆኑ ብቻ ነው። ተክሌ የከፈለው መስዋእትነት ትልቅ መፀሃ ፍ ይወጣዋል። ታዲያ ይህን ታላቅ የአማራ ህልውና ታጋይና ፋና ወጊ ትቶ አማራውን ለሚያሻሽጠው ታማኝ ነበር የአማራው ምድር ያረገደው። ወዳጅና ጠላትን አለማወቅ ይሉሻል ይሄ ነው።

  አንባቢዬ ሆይ ይህንን ስጠቅስ በተክሌና በታማኝ መሃከል ጠብ ለመዝራት እንዳልሆነ በደንብ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ። ነገር ግን እውነቱ መነገር ስላለበት ነው። የአማራው ወጣት በሰከነ ልብ በዳያስፖራውም ሆነ በሃገር ውስጥ በቀውጢው ሰአት ጎኑ የቆሞቱን እውነተኛ ታጋዮች ማወቅ ግዴታው ነው። እንደ እውነቱ ለማናገር ሃገር ቤት ውስጥ ያለው የአማራ ህዝብ የግንቦት 7 ቶችና የታማኝንም የፖሊቲካ አቁዋም በደንብ ጠንቅቆ ያውቃል። አለመታደል ሆኖ አማራው ሁልጊዜ የመዘናጋትና ከሞኝነት የሚቆጠር የዋህነት ያጠቃዋል መሰል ለታማኝ በየነ ኮስታራ ፊትና ለዘብተኛ አቀባበል ማድረግ ሲገባው እልልታና እስክስታ ይዞ ነበር የተቀበለው። መቼም የባሰ አታም ጣ ነውና ይሀው የዋህ ህዝባችን ብርሃኑ ነጋንና አንዳርጋቸው ፅጌንም በፈረስና በርችት እንዳይቀበላቸው ያስፈራኛል። በሬስ ከአራጁ ይውል የለ ????!!!!! ።

  ቸር ይግጠመን

  ንቁ እንንቃ የደብረብርሃ

  « Back to archive
 • Leave your comment

 • Name:
   
  Email:
  Comment   
  captcha
  Enter the code shown above: