• News

 • ተቃውሞና ድጋፍ ገደብ ካጣ፣ያመጣል ጣጣ 26 November 2018 | View comments

 •  እሥከዳር በላቸው

  ተቃውሞና ድጋፍ ገደብ ካጣ፣ያመጣል ጣጣ ! የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግስት ቅጥ ባጣ ተቃውሞ ሲወድቅ፣ ገደብ ባጣ ድጋፍ የደርግ መንግሥት መጣ።“ ከደርግ የባሰ አረመኔ አይመጣም ” በሚል ቅጥ ባጣ ተቃውሞ ደርግ ሲወድቅ፣ ገደብ ባጣ ድጋፍ ትነግ መጣ።

  የተጠላው የትነግ | ኢሕአዴግም ሥርዓት፣ከደርግ የባሰ አረመኔ ዘረኛና ዘራፊ በመሆኑ፣ ህብረተሰቡ ገደብ የለሹን በደል ፣ ጥላቻን ባረገዘ ተቃውሞ ቢታገለውም፣ “ ሞተ ” የተባለውን ሥርዓት የኢሕአዴጉ ጠቅላይ ሚኒስቴር በጥገናዊ ለውጥ ሽንገላ ለጊዜውም ቢሆን ነፍስ እንዲዘራበት ለማድረግ ችሏል።

  ዛሬም እንደትናንቱ ከትነግ | ኢሕአዴግ የባሰ አይመጣም ብለን ለ ገደብ የለሽ ድጋፍ የዶክተር አቢይ “ ኦዴግ | ኢሕአዴግ ” ላይ ወደ ቅን። ቀደም ሲል አማራው ትግሬዎችን አጅቦ ደርግን ከጣለ በኋላ፣ትግሬ አማራን ክዶ እንደመታው ጠንቅቆ ቢያውቅም፣በእነኦነግና ኦህዴድ እንዳሥመታው ግን የዘነጋ ይመሥላል።

  በመሆኑም ዛሬም አማራው ! በትነግና በኦሮሞዎች መካከል በሚደረገው ግብ ግብ ውስጥ ኦሮሞዎችን አጅቦ ሥልጣን አሥይዟል። ይህም ለጊዜው ካዋዛን በኋላ ምን እንደሚያመጣ ማወቅ አይከብድም።

  አዲስ አበባና ቡራዩ ላይ የኦነግ ቄሮዎች የሠሩትን ልብ ይ ሏል። ንፁሀን አማራዎችን በበደኖ በወለጋ፣በአርሲ ወዘተ የጨፈጨፈው ተገንጣዩ ኦነግ፣ ” በዘር ማጥፋት ወንጀል ” ወደእሥር ቤት ከመሄድ ይልቅ ፣እየተለመነ፣ ከለማ ጋር በምን እንደተስማሙ እንኳን ሳይገለፅ መሥማማታቸውን ነግረውናል።

  በአንድ በኩል በትግሬዎቹ ቦታ ኦሮሞዎች እየተተኩና አዲስ አበባንም በኦሮሞ ባለሥልጣናት እያጥለቀለቁ፣ ” መልሶ ለመገንባት ” በሚል፣የአማራውን እና የሌሎችን ብሔሮች ቤቶች እያፈረሱ፣ሕዝ ቡን ሥራፈት እያደረጉ፣ ” ጫት ቃሚው በዛ ” እያሉ ይሳለቃሉ። እነለማ መገርሳም አዲስ አበባን በቁጥርም ይሁን በአሥተዳደር በኦሮሞ የበላይነት ለማጥለቅለቅ፣ካላቸው ዓይን ያወጣና የረቀቀ የዘረኝነት በሽታ በመነሳት፣ ቄሮዎች ! ለአዲስ አበባ ከሚቀርበው ከምዕራብ ሸዋ ያፈናቀሉት አማራ በአዲስ አበባ አልፎ ወደራያ ተሰዶ፣ በርሀብና በቸነፈር ሲሰቃይ ፣ ” በሶማሊና በኦሮሞ መካከል ችግር ሥለተፈጠረ ” በሚል ኦሮሞችን ከሩቅ እያመጡ አዲስ አበባ ያሠፍራሉ።

  በሌላ በኩል “ እኛ ” በ 27 ዓመቱ ከልክ ያለፈ በደል ምክንያት፣በወንጀለኞች ላይ የሚሠራውን ብቻ መሥማት በመምረጣችንና ለቀጣዩ አደገኛው አካሄድ ዓይናችንን በመጨፈናችን፣ አቅጣጫ የሚያሥቱ ማዘናጊያዎች ብቅ ባሉ ቁጥር ሳናሥተውልና ሳናገናዝብ፣ “ ደግ አደረገልን ” እያልን እልልታውን እናቀልጠዋለን። የዚህ ሁሉ ችግር የህብረተሰቡ አለመንቃትና ከመጣው ጋር የመለጠፍና ያላንዳች ገደብ መ ደገፍ ነው። “ በሬ ሆይ ! በሬ ሆይ ! ሣሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ ” እንዳይሆን ” ቆቅ እንሁን 2 እንንቃ ” እላለሁ።

  ከመጣው ጋር ያላንዳች ጥያቄ ገደብየለሽ ድጋፍ እየሠጠን መጨረሻው የራሳችን መጥፊያ እንዳይሆን ከጅምሩ ድጋፋችን ገደብ ኖሮት ፣ሥህተቶች ብቅ ሲሉ ወዲያውኑ እንዲታረሙ ጫና በማድረግ፣ እያሥተዋልን እንጓዝ። አቢይ ከመጣም ወዲህ ቢሆን መጠኑ ይለያይ እንጅ በወልቃይት፣በራያ፣በቤኒሻንጉል፣ በቡኖ በደሌ፣በም ዕራብ ወለጋ፣በድሬደዋ፣በሐረር፣በአዲስ አበባ ወዘተ በአማራው ላይ ግድያው፣መሳደዱና መታሰሩ አለመቆሙን ለመገንዘብ አይከብድም።

  ነገ የአማራው ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ራቅ አድርገን የማየትና በጥልቀት መረዳት ከቻልን፣የአማራውን ትግል እሥከድል ማጠናከር እንድምንችል አያጠራጥርም ። አማራው ንቃ ! አማራው እንዳይደራጅና እንደተለመደው ተከታይ እንዲሆን የሚደረጉ የማዘናጊያ ታክቲኮች ! (1)” አገር እንዳይበተ ን ” የሚሉት አነጋገር እንደተለመደው አማራውን በማሥፈራራት የቆራጭ ፈላጭን ቡድን ዕድሜ እያጀበ እንዲያራዝም ታስቦ ነው። አዎን ! አገር በ 1983 ዓም ተበትኗል።

  ዛሬም ወሬ ነው።የተበተነውን የሚሰባስበው ደግሞ አማራው ገብቶት አንድ ሆኖ ሲታገል እንጅ ባሥፈራሩት ቁጥር ካፈገፈገ ተጎጅ ራሱ እንደሆነ ይገንዘብ።

  (2) ሌንጮ ለታ ! “ ሕዝብ ( ኦሮሞ ) የመረጠውን ትቀበላለህ፣የብሔር ጥያቄ ላይ ነርቨስ አንሁን ” ብሎናል ። “ ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት ” እንዲሉ ነው።

  (3) ብርሀኑ ! ” ለሁሉም እኩል የሆነች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንገባ ” ይለናል። ይህን ቧልት የሚነግረን በዘርና በቋንቋ ብትንትኗ የወጣች አገር ላይ ቆሞ ነው።ማፌዝ አይበቃም ???

  (4) ጠበንጃ ይዘው በዘር ከመጡ ቡድኖች ጋር በመወዳደር ሥለ ዴሞክራሲ መለፈፍ “ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ” እንደሆነ ይታወቅ።

  (5) በጅዋር ሚዲያ በኦሮምኛ ጣሂርና ሄኖ ክ ጋቢሳ የሚባሉት ጉዶች እንዲህ ይላሉ፣ “ ሀበሾች አማሮች ኦሮሞን በተንኮል ላለፉት 130 ዓመት አባረው በከተሞች በድሬደዋ፣ በአዳማ፣በፊንፊኔና በሀረር ይኖራሉ፣።ኦሮሞ የሚኖረው በድንበር ነው።በከተማም ለመኖር ከሀበሻ አማራ ተከራይተን ነው።ሥለዚህ ወንድማችን ታከለ ኡማ በሚመጣው ምርጫ ላይመረጥ ይችላልና እሥከዚያው ከተሞቻችንን መልሰን በእጃችን ማድረግ አለብን።ጊዜ የለንም ።

  ከምርጫው በፊት በእጃችን ለማድረግ መፍጠን አለብን። የእነዶክተር አቢይም ድርጅት ፊንፊኔንና ድሬድዋን ለማሥመለስ ሲሠሩ ረብሻ ከተነሳ “ ማሰር ” ይኖርባቸዋል። አሜሪካኖችም እኮ ምንም ዴሞክራት ቢሆኑ ሁሉንም ነገር በዴሞክራሲ አይሠሩም። ትግሬዎችም ከቢሮ ይባረሩ። “ ይህን ምሥኪን አማራ ከትግሬ ዘረኞች ወደኦሮሞ ዘረኞች እየተቀባበሉት ነው እንዴ ” ያሠኛል። ምንም ተባለ ምን እኛ አማራዎች ወደዋናው መፍትሄ እንግባ!

  (1 ኛ ) የአማራው ወዳጅ ራሱ አማራው ብቻ እንደሆነ እና ሌላ ወዳጅ እንደሌለው ተረድቶ፣ራሱ በራሱ ተጠናክሮ በሁለት እግሩ መቆም እንዳለበት ራሱን ያሳምን። ከልቡ ራሱን ማሣመን ሲችል ብቻ ነው ለማንነቱ የማይበገረው። 

  (2 ኛ ) ያዝ ለቀቅ ያለ ትግል አክትሞ አንድ ቋሚ አካሄድ ይኑረን።ጠላቶቻችን አዳዲስ የቤት ሥራ በሰጡን ቁጥር በእርሱ ላይ አላሥፈላጊ ጊዜያት ሥለምናጠፋ ጭንቅላታችን ለአማራው ትግል የሚጠቅሙ ነገሮች ለማፍለቅ ጊዜ አያገኝም።ለምሳሌ ሥለአቢይ፣ሥለ ኦነግ ፣ሥለትነግ ወዘተ ሥናወራ ጊዜ አናጥፋ ።

  (3ኛ) አቢይ መርቶና ታግሎ ነፃ እንዲያወጣን የምንጠብቅ ብዙዎች ነን።ይህ ሥህተት ነው።በራስህ ላይ ተማመን። እያንዳንዳችን “ እኔ ራሴ እንደግለሰብ ምን ባደርግ ነፃነቴን ተግባራዊ አደርጋለሁ ” ብለን እንጠይቅ። (4ኛ) “ ይህች ዓለም የምታጅበው ጉልበት ያለውን ብቻ እንደሆነ ተረድተን ” አሁን የጀመርነውን መሰባሰብ ይበልጥ በማጠናከር፣ያልሞከርነው የትግል አካሄድ ካለ በመቃኘት፣የድርሻችንን ለማግኘት በተለያዩ የትግል መንገዶችና ዘዴዎች ተጠናክረን መብታችንን በእጃችን ማድረግ የግድ ነው።ከዚህ ውጭ ሌላ አቋራጭ መንገድ የለም።

  (5 ኛ)አማራው በተገለለበትና ባልተሳተፈበት፣ የኢትዮጵያን አንድነት ንዶ “ 9 የዘርና ቋንቋ ክልሎች ፌደራሊዝምን ያዋቀረው ህገ መንግሥት፣ በ 1983 ዓም ኮንፈረንስ እንደፀደቀ፣ ትነግና ኦነግ የዝሆኑን ድርሻ መሬቶች ከአማራው በመቀማት ርስት አልባና ተባራሪ በማድረግ አጣብቂኝ ውስጥ ማሥገባታቸው ገሀድ ነው።

  ይህ ዛሬ ያለው ዘርን መሠረት ያደረገው ህገ መንግሥት ከ9 የዘርና የቋንቋ ከፋፋይ ፌደራሊዝም ጭምር ፈርሶ ፣ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተዋቀረ ከዘርና ከቋንቋ የፀዳ ለአሥተዳደር የሚመች በጥልቀት የተጠና ሕዝብን ከሕዝብ የሚያቀራርብና የሚያስማማ፣ እኩልነትንም የሚያሟላ ፣እንደ እነአሜሪካም ይሁን እንደ እነሥዊዝ ወዘተ ለምሳሌ “ አካባቢያዊ ፌደራሊዝም ን ባካተተ ህገ መንግሥት” ሲተካና በአፍና በወሬ ሳይሆን ከልብ አብሮነታችንን በተግባር ሥናረጋግጥ ብቻ ነው።

  ይህ ተግባራዊ እንዳይሆን ትነግና ኦነግ እንዲሁም ሌሎች አክራሪዎች! ዛሬም ድረስ በአማራ ላይ ግድያ ከመፈፀምም አልፈው በጠቅላላ በአገሪቱ ውስጥ ቀውስ እንደፈጠሩ ነው። ምክንያቱም የሠረቋቸው መሬቶች ወደባለቤቶቹ እንዳይመለሱባቸውና አማራውንም ረግጠው ለመኖር።

  ማሳሰቢያ !እሥከዛሬ የአማራው በተናጠል መሄድ አሥጨርሶታል፣ተፈናቃይ አድርጎታል። ከእንግዲህ “የአማራው አንድነት ለህልውናችን ዋሥትና” ሥለሆነ አማራው በአንድነት እንዲቆም የአማራው ሕዝብ ጫናና ግፊት ያድርግ። አንድ የማይሆኑ ከሆነ ሕዝቡ ዕርዳታውንና ድጋፉን ያንሳ! መፍትሄው ይህ ብቻ ነው። ታግሎ ህልውናን ማሥጠበቅ የተፈጥሮ ህግ ነው!

  እሥከዳር በላቸው

  « Back to archive
 • Leave your comment

 • Name:
   
  Email:
  Comment   
  captcha
  Enter the code shown above: